ከንቱ ኢትዮጵያዊ ነኝ (በእሸቱ ታደሰ)

ከንቱ ኢትዮጵያዊ ነኝ

በእሸቱ ታደሰ

እዕምሮዬ ዛለ ልቤንም ጨነቀኝ
የማረገው አጣሁ ሆዴን ባር ባር አለኝ
ባስብ ባሰላስል ብጓዝ ተቀምጬ
ጠብ እንኳን አላለ ባይም አንጋጥጬ
እኔ አንድ ሰው ነኝ
ተስፋ እንኳ የራቀኝ
የወገኔን ሲቃ ሞቱን እያየሁኝ
ካጠገቡ ቆሜ መከታ ያልሆንኩኝ
ነፃነት ፍለጋ አደባባይ ቢቆም
ፍትህን ለማግኘት ለመብቱ ሆ ቢልም
በጠራራ ፀሃይ ግንባሩን ተመቶ
ወድቆ ከመንገዱ ልቤም አይኔም አይቶ
ከማልቀስ በስተቀር
ከማለት ነፍስ ይማር
አንዳች ያልፈጠርኩኝ
ከንቱ ኢትዮጵያዊ ነኝ

Post a Comment

0 Comments