ከአንድ ወር በፊት ለማሳየት እንደሞከርኩት ኃይለማርያምን መተካቱ ኃይለማርያምን እንደማባረሩ ቀላል አይሆንም የሚል ነበር። አሁንም ሁኔታው ከዚያ ውጭ እንዳልሄደ ለሁሉም ግልጽ ይመስለኛል።
የምዕራባውያን ምርጫ
ምዕራባውያን ወያኔ ወንበሩን ለአብይ ቢሰጥ ብለው የሚጎተጉቱት "ድርሻየ በቁመናየ ልክ አይደለም" ብሎ ማእበል ያስነሳውን ኦሮሞ ያረጋጋል። በዚህም መንግስት የተወሰነ የጽሞና ግዜ እንዲኖር አስተዋጾ ያደርጋል በሚል እሳቤ ሲሆን ሌላው ተቃዋሚ ደግሞ ለአብይ የተሻለ ቀና አመለካከት ያሳየውን ያህል አገሪቱ የሚያስፈልጋት ስርነቀል ለውጥ በመሆኑ የአብይ ወደ ስልጣን መምጣቱ ችግሩን ላይፈታው ትግሉን ሊያዳክመው ይችላል የሚል ፍርቻ አንቆ ይዟቸዋል።
ሂደቱ በራሱ ገፍቶ አብይን ወደ ስልጣን ቢያመጣው
- ካቢኔቱን አፍርሶ እንደ አዲስ ከመሰየም ጀምሮ በውስጥም በውጭም ለሚገኝ ተቃዋሚ ጥሪ ማቅረብን፣ ለእስረኞች ምህረት የማድረግን፣ የሽጝግር መንግስት ምስረታ ላይ በጎ ፍላጎት ማሳየትን የመሳሰለ እርምጃ መውሰድ ቢጀምር ከመፈንቅለ መንግስት በመለስ እንዴት በሰላማዊ መንገድ ማስቆም እንደሚችል ወያኔ እራሱ እርግጠኛውን መንገድ አለማወቁ ሲሆን
- ወያኔ ምናልባት ተሳክቶለት አብይን በጠሚሩ ወንበር ላይ አስሮ እንደሃይለማርያም የፈለገውን ለማስፈጸም ቢቻለው የአዲሱ የቆሬ ጀነሬሽን ምን ሊያስከፍለው እንድሚችል ሂሳቡን ማስላት አለመቻሉ ነው።
በመሆኑም አንድ ግዜ አብይ ወደ ስልጣን መጥቶ ስጋት መሆን ቢጀምርና ወታደሩ ወደ ኩዴታ ውስጥ እንዲገባ ቢገደድ በአለም አቀፍ ደረጃ ሊያስከትልበት የሚችለውን የፖአቲካ ቀውስ መቋቋሙ ከባድ ሲለሚሆንበት ለህወሃት ቀላሉ መንገድ ከወዲሁ በምክያት እንዳይመረጥ ልዩ ልዩ ሳንካ መፍጠር የተሻለው አካሄድ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱን እያየን ነው።
ሌላው አዲሱ ያልተጠበቀው አሰላልፍ ቁጥራቸው ውሱን የሆኑ የደቡቡ ዴህዴን ሰዎች ድምጻቸውን ለዶር አብይ የመስጠት ዝንባሌ ማሳየታቸው ቀጣዩን አሰላልፍ እንቆቅልሽ አድርጎታል።
ሌላው አዲሱ ያልተጠበቀው አሰላልፍ ቁጥራቸው ውሱን የሆኑ የደቡቡ ዴህዴን ሰዎች ድምጻቸውን ለዶር አብይ የመስጠት ዝንባሌ ማሳየታቸው ቀጣዩን አሰላልፍ እንቆቅልሽ አድርጎታል።
0 Comments