በዘራቸውና በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት በብዙ ዜጎች ላይ በደል ሲፈፅም የምናውቀው "የኢትዮጵያ አየር መንገድ" ሰሞኑን ደግሞ አዲስ ርዕስ ሆኖ ስለመጣ "አንተም ሰለባ ነበርክና እስኪ የምታውቀውን ለህዝብ አድርስ" በማለት ብዙ ጓደኞቸ ስለጠየቁኝ በሌሎች የስራ ባልደረቦቸ ላይ የደረሰውን ለሌላ ጊዜ ላቆየውና እኔን ያጋጠመኝን በአጭሩ ከሰነዶች ጋር አያይዤ ላቅርብ።
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ" "ዜጎችን በዘራቸው እየለየ እና የፖለቲ ቁንጮውን ህወሃትን የሚቃወሙትን እየሰለለ ልዩ ልዩ በደል ያደርሳል" እየተባለ ለሚቀርብበት ክስ ለማስተባበል "በሰራተኞቹ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች በህግና በደንብ መሰረት ብቻ እንደሆነ እየነገረን ይገኛል። ይህ ማስተባበያ ሃሰት እንደሆነ ለማሳየት በእኔ የደረሰውን እንደ አንድ ማስረጃ መውሰድ ይቻላል።
እ.ኤ.አ በ2011 "ለአባይ ግድብ ገንዘብ የምናዋጣበትን ሁኔታ ለመወያየት በስብሰባ እንድትገኙ" የሚል መልዕክት ድርጅቱ በሰጠኝ "ኢ-ሜይል ደረሰኝ። እኔ ስብሰባ መሳተፍ እንደማልፈልግ፣ ገንዘብም ካለእኔ ፈቃድ ከደመወዜ እንዳይቆረጥ ይህን ካደረጋችሁ በህግ እንደምጠይቅ ጠቅሼ በዚያው መልዕክቱ በመጣልኝ ኢ-ሜይል ምላሽ ፃፍኩ።

ይህም "የኢንዱስትሪ ሰላም ለማናጋትና ሰራተኛውን ለማሳመፅ" የሚል ታርጋ ተሰጥቶት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያባርር ደብዳቤ አመጣልኝ። ከሁለት ዓመት በላይ ክርክር በስር ፍርድ ቤት የተረታው "አየር መንገድ" እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይግባኙን ውድቅ አድርጎ ወደ ስራዬ እንድመለስ ተወሰነ።
ነገር ግን በፍርድ ቤት ያልሆነላቸውን ለመበቀል ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በማቀድ ቀድሞ ስሰራበት ወደነበረው ክፍል ሳይሆን ፈፅሞ ከእኔ ስራ ግንኙነት ወደሌለው ክፍል "ሱፐርቫይዘር" ሆነህ ተመድበሃል የሚል ደብዳቤ ተሰጠኝ።
ወደ ስራ ተመልሸ በአየር መንገዱ በቆየሁበት አንድ አመት ከአምስት ወር ውስጥ በርካታ ትንኮሳዎችና ተማርሬ በራሴ ለቅቄ እንድሄድ የሚያደርጉ ሸፍጦች አጋጥመውኛል። በመጨረሻም "ከስርህ የሚሰራ ሰራተኛ ጥፋት አጥፍቶ እያለ አፋጣኝ እርምጃ አልወሰድክም" ተብዬ ከስራ ለሁለተኛ ጊዜ ተባረርኩ። አሁን እንዴት በህግና በደንብ መስረት እንደተሰራ እንመልከት።
ነገር ግን በፍርድ ቤት ያልሆነላቸውን ለመበቀል ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በማቀድ ቀድሞ ስሰራበት ወደነበረው ክፍል ሳይሆን ፈፅሞ ከእኔ ስራ ግንኙነት ወደሌለው ክፍል "ሱፐርቫይዘር" ሆነህ ተመድበሃል የሚል ደብዳቤ ተሰጠኝ።
- የእኔ ጥፋት ሆኖ የተቆጠረው ሰራተኛው እ.ኤ.አ ጥቅምት 1 ቀን 2014 ጥፋት አጥፍቶ እያለ እስከ ጥቅምት 20 ቀን ድረስ እርምጃ አልወሰድክበትም" ነው። (አንደኛውን ደብዳቤ ተመልከቱ)
- ነገር ግን ጥፋት አጠፋ የተባለው ሰራተኛ እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2 ቀን 2014 ጀምሮ ከስራ ታግዶ እንደቆየና ጥፋቱም ተመርምሮ ከስራ የሚያባርረው ባለመሆኑ ወደስራው መመለሱን ያሳያል። (ሁለተኛውን ደብዳቤ ተመልከቱ)
- አቶ ተወልደ ገ/ማርያም እኔን ለማባረር ሰራተኛው ያጠፋው ጥፋት ትልቅ እንደነበርና በድርጅቱም ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ቢገልፅም (ሶስተኛውን ማስታወሻ ተመልከቱ) ሰራተኛው አጠፋ የተባለው ግን ተጣርቶ ቀላል እንደነበር በራሱ በአየር መንገዱ ተወስኖ ሰራተኛው ወደ ስራው እንዲመለስ ተደርጓል። (ሁለተኛውን ደብዳቤ ተመልከቱ)
- አቶ ተወልደ "ሰራተኛችን በዘራቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው አናጠቃቸውም" ቢሉም የፖለቲካ ተሳትፏችን እየተሰለለ ለማባረሪያነት ይጠቀሙ እንደነበረ አየር መንገዱ እኔን አስመልክቶ ሳያፍር ለፍርድ ቤቱ የፃፈውን አራተኛውን ደብዳቤ ተመልከቱ።
በአጠቃላይ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ" ምን ያህል በተበላሸ፣ በወንጀለኞችና በአናሳ የህወሃት የስለላ መዋቅር የሚገዛና ይህንን አገዛዝ ይቃወማሉ ያሏቸውን ሰዋች በስራ እድገትና ምደባ ከመበደል አልፈው እስከማሳሰርና ማባረር ድረስ ግፍ የሚፈፀምበት ተቋም እንደሆነ በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።
0 Comments