ዶክተር ዲማ የነበረውን እውነት እንዲህ በመናገራቸው ሳላመሰግናቸው አላልፍም – አቻምየለህ ታምሩ

ዶክተር አብይ አሕመድን  «የኦሮሞ ተወላጅ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር» እያሉ  የሚያስተጋቡ  ደጋሚዎችን  ስህተት  ከሳምንታት በፊት «ወሬ ሲነግሩህ ሀሳብ ጨምርበት»  በሚል ባተምነው ጽሁፍ  ስናርም መቆየታችን ይታወሳል።
ከታች የታተመው ቪዲዮ ዶክተር ዲማ ባንድ መድረክ ላይ ያቀረቡት ንግግር ነው።
ዶክተር ዲማ ነገዖ ከኦቦ ሌንጮ ለታ፣ ከዶክተር ጌታቸው በጋሻውና ከሻለቃ ዳዊት ጋር በመሆን  Gabataa Media ላይ ቀርበው  ባካሄዱት  ውይይት ላይ የተናገሩት እውነት ሰሞኑን አንዳንድ ግለሰቦችና የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ጭምር ሆን ብለው በሚመስል መልኩ እየደጋገሙ የሚያስተጋቡትን ውሸት በድጋሚ የሚያጋልጥ ነው።
እኔም ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በዶሴ እንደሞገትሁት፤ ይኸው ዶክተር ዲማም ስለኖሩበት ዘመን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በደርግም ሆነ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኦሮሞ ተወላጆች የሆኑ ጠቅላይ ሚንስትሮች ነበሯት። ዶክተር ዲማ የነበረውን እውነት እንዲህ በመናገራቸው ሳላመሰግናቸው ማለፍ አልሻም።
ከላይ የታተመው የዶክተር ዲማ ንግግር ሙሉ በሙሉ የምስማማው ዶክተር አብይ የመጀመሪያው የኦሮሞ ተወላጅ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አለመሆናቸውን ስለተናገሩት ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ጠቅላይ ሚንስትር መሆን ስላለበት በተናገሩት አስተያየትም ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ።
ይቺን የዶክተር ዲማን ንግግር ግን «Ethiopia will have its first ethnic Oromo Prime Minister» እያለ በተደጋጋሚ ለሚጽፈው ለሎንዶኑ  አባላትም እንኳ ቢሆን የተሳሳቱትን ስናይ  የምንተቸውን ያህል እውነት የሚናገሩትን ስናገኝ ደግሞ እንዲህ እንደ ዶክተር ዲማ እውነት በመናገራቸው እናመሰግናቸዋለን።
ይቺን የዶክተር ዲማን ንግግር ግን ስለ ዶክተር አብይ በጻፈ ቁጥር «Ethiopia will have its first ethnic Oromo Prime Minister» እያለ በተደጋጋሚ  ለሚጽፈው ለሎንዶኑ Awol Kassim Allo ጋብዙልኝ።

Post a Comment

0 Comments