- "ብአዴንና የሚመለከታቸው አካልት ቀንበሩን ሰብረው ከተነሱ አይቀር፣ ጨለማውን ገፍፈው ብርሃን ካመጡ አይቀር፣ስብሰባውን ትክክለኛና ውጤታማ አድርገውት ከተነሱ አይቀር መደምደሚያው መሆን ያለበት ተከዜ ላይ አብረን ውሃ መጠጣት አለብን። ሌላ ነገር አይደለም። በፍትህ!"
- "ወጣቶቹ የመጡበት ምክንያት እኛ አማራ ነን ብለው አማራነታቸውን በዘፈን፣ በሀዘን፣ በአለባበስ፣ በበዓል አከባባር ……የፋሲል ከነማ ቲሸርትን፣ የዶክተር አብይ አህመድ ቲሸርትን ለብሶ ወንጀለኛ ነህ የተባለ አለ። ባህሉን መግለፅ አትችሉም እየተባሉ ተከልክለዋል"
- "ብዙ አድራሻቸው ያልታወቁ ወጣቶች አሉ። በእስር ቤት 40 ወጣቶች አሉ። አምስቱ ሴቶች ናቸው። ሌሎች አድራሻቸው ያልታወቀ አሉ።"
- "ለውጠነዋል፣ ከአሁን በኋላ በእኛ ነው ያሉት ወጣት ነው ባህሉና ማንነቱ ሲነካ አፈንግጦ የወጣባቸው።"
- "በአማርኛ ለመማር የተከለከሉ፣ በአማርኛ መናገር የተከለከሉ፣ በአማርኛ ደስታ እና ሀዘናቸውን መግለፅ የተከለከሉ፣ በአካባቢያቸው መልበስ የሚገባቸውን ልብስ እንኳ የተከለከሉ ወጣቶች አሻፈረን ሲሉ ልዩ ኃይል በማምጣት በመደብደብ፣ በማሰር፣ በማሸማቀቅ ቀደም ሲል ህወሓት የተለማመደበትን ተግባር አሁንም እየቀጠለበት ነው ያለው። አማራ ነኝ ማለት ለእሱ ጠላት ነው።"
- "ወጣቱ የሚለው ተወልደን ባደግንበት ሀገር በትምህርት ተበድለናል፣ ባህላችን ታፍኗል፣ ማንነታችን የመጨረሻዋ መታወቂያችን፣ አማራ ነኝ የምትለዋን ለመንጠቅ ከፍተኛ ወረራ፣ ድብደባ፣ ግድያ፣ እስራት፣ የበረታብን ሰዎች ነን ነው"
- "መንግስት እንደ ፌደራል፣ እንደ አማራ ክልልም ለዚህ ሕዝብ ምላሽ እንዲሰጥ መልዕክት እናስተላልፋለን። ከዛ አካባቢ መንግስት ቢኖር ሕዝብን አያሳድድም ነበር። ……አመፅ ነው ያለው። ሕጉም የለም። መንግስትም የለም ለማለት የሚያስደፍር ስራ እየተሰራ ነው"
- " በአባታቸው መሬት፣ በአባታቸው ባድማ ሰርተው ደሞዛቸው አይከፈላቸውም። ብዙዎች ሰርተው ተባርረዋል። ብዙዎቹ ሰርተው ከሚገነባ ቤት ተወርውረው ወድቀዋል። በጃናሞራ፣ በበየዳ እንኳን ያሉት ትግራይ ሄደው ስራ ሰርተው ከፎቅ ተወርውረው የሞቱ ሰዎች አሉ። ይህ በማስረጃ በቅርቡ ይመጣል። ስም ዝርዝራቸውን እናቀርባለን።"
- "ወልቃይትን የሚፈልጉት ምድሩንና ሴቶቹን ነው"
- "አማርኛ የሚባል ቋንቋ የለም ይሉናል"
- "አማራ ነን ስላልን ብዙ በደል ደርሶብናል"
- "ወልቃይት ውስጥ ሀዘን እንኳ መግለፅ አንችልም። ተከልክለናል……የእኛ አባቶች ደግሞ ግጨው በሚባል በርሃ ሄዳችሁ ካልሰለጠናችሁ ምሽግ ካልያዛችሁ እየተባሉ መሳርያቸውን እየተቀሙ ነው"
- "በሏቸው ካልተደበደቡ ካልተገደሉ አይለቁም እየተባልን ሌት ተቀን ነው የምንደበደበው። አማርኛ ስለተናገርን።"
- "የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ ያረጋጋልን። ካልሆነ መኖርያ የለንም።"
- "ጓደኛዬ የአብይን ስቲከር ለጥፎ ስለነበር በመኪና እያራወጡ ገጭተውታል። ሶስት ጥይት ተኮሰው ስተውት ነው የገጩት"
- "ጠፍተው የቀሩ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች አሉ። እነ ማማዬ አንጋውም በልዩ ሀይል አንገታቸው ተቀጭቶ በግልፅ ሞተዋል። በእነሱ አጎበር ላይ ብዙ ሰዎች መሳርያቸውን ተዘርገዋል። ተደብድበዋል።"
- "አማራ ተከዜ ቀርቶ፣ ብድብዴ ተሻግሮ እርፍ አይቆርጥም፣ ከተሻገረ እንዋጋለን፣ ታጠቁ፣ ሰልጥኑ" ተብለን "እኛ አማራ ነን አማራን አንወጋም፣ አንሰለጥንም" አልን።
- "ከበው እጅህን ስጥ አሉኝ። ገሎ መሞት እንጅ እጅ መስጠት ባህላችን አይደለም ለአማራ ሕዝብ፣ ለወልቃይት ሕዝብ፣ እኔ አልሰጥም እሞታለሁ ብየ ቦታ ይዤ ስቀመጥ ሚሊሻውም፣ ህዝቡም፣ ሀገሩም ደረሰ"
- "ሰራተኛ ውል ገብቶ በአማርኛ ተፅፎ ወደ ክስ ሲገባ "ወደ ትግርኛ ቀይራችሁ አምጡት፣ አማርኛን ልናጠፋ እየጣርን ነው ብለው ሶስት መቶ፣ አራት መቶ ብር ከፍሎ ነው አማርኛን ወደ ትግርኛ የሚተረጎመው።"
- "እኔ ሕዝባዊ ሚሊሻ ነኝ። ከመንግስቱ ጋር ያለያየ ማንነታችን አማራ ነው የሚሉትን እኛን አይወክሉም ብላችሁ በሉ ስንባል አይደለም እኛ አማራ ነን አልን። ማንነታችን አማራ መሆኑን ዘጠኝ ክልል ቀርቶ፣ ዘጠኝ ሽማግሌ ከልሎ ይሰጠናል። ርስታችን ነው፣ ማንነታችን ነው። እስከ 83 ዓመተ ምህረት በጎንደር ክፍለ ሀገር፣ በዳባት አውራጃ ነው ስንተዳደር የነበረው። ቅስና ይሁን ድቁና እንደ ሀይማኖታችን ስናመጣበት የነበረው ጎንደር ክፍለ ሀገር፣ ዳባት አውራጃ ነው። እኛ አማራ ነን። ይህ ነው ሊያለያየን የቻለው።
- "አማራ ተከዜ ቀርቶ፣ ብድብዴ ተሻግሮ እርፍ አይቆርጥም፣ ከተሻገረ እንዋጋለን፣ ታጠቁ፣ ሰልጥኑ" ተብለን "እኛ አማራ ነን አማራን አንወጋም፣ አንሰለጥንም"አልን። "ይህን የማታደርጉ ከሆነ መሳርያችሁን ታራግፋላችሁ (ታወርዳላችሁ) ተባልን፣ "ሕዝብ ነው የሰጠን" አልን። በዚህ ላይ ቅዋሜ እያለን ቆየን።
ከዚህ መሃል ተኩስ ተታኮሱ። ሲታኮሱ ልዩ ሀይሉ ተመታ። እኔ ቤት እያለሁ ሕዝብ እየዘለለ ገባ። ልዩ ሀይሉ ሲደግንብኝ እኔም መሳርያ አውርጄ ልቡ ላይ ደገንኩበት፣ ቆመ። ከዚህ በኋላ ከበው እጅህን ስጥ አሉኝ። ገሎ መሞት እንጅ እጅ መስጠት ባህላችን አይደለም ለአማራ ሕዝብ፣ ለወልቃይት ሕዝብ፣ እኔ አልሰጥም እሞታለሁ ብየ ቦታ ይዤ ስቀመጥ ሚሊሻውም፣ ህዝቡም፣ ሀገሩም ደረሰ። ይህን ልጅ ከባችሁ አትግደሉት።
የሚገድለውን አይተናል ብለው እነ ካሳ ብሩ ተናገሩ። "በል እንፈልግሃለን፣ ምስክርነት" ብለው አሸብር ተቀብሎ ገሬ ለሚባል ፖሊስ ሰጠው። ሊመሰክር ሄደ። ምንድን ነው ያየኸው ሲሉት "አዳነ አልገደለም፣ ራሳቸው ልዩ ኃይሎች ሲታኮሱ ልዩ ሀይል ነው የመታው" ሲል፣ "ምን አባህ እንዲህ ብለህ ትመሰክራለህቀጥቅጠው?" ብለው ቀጥቅጠው፣ሰባብረው ጣሉት። ጎንደር ሆስፒታል ይገኛል።
ከዚህ በኋላ ማንነቴን ሕገ መንግስት ይመልስልኛል። እሰዋለሁ፣ እጅ አልሰጥም፣ የተበተነ ንብረት ይበተን ብዬ ያን ጊዜ እንደወጣሁ በዳንሻ ዙሪያ በጫካው ሰንብቼ ወደዚህ ስደውል "ና" እንደናንተ ያሉ ሰዎች አሉ ማንነትክን ጠይቅ ሲሉኝ መጣሁ።
አሁንም ባድማችን አንለቅም። ባህላችንም አይደለም። መንግስትም እንዲያውቅልን። ሄደን ብንሞትም ከቤተ ክርስትያናችን፣ ከደብራችን መቀበር እንጅ በስደት አንቆምም። ……ማንነታችን ዛሬም አማራ ነው። ነገም አማራ ነው።
መጀመርያ ጊዜ ክልል 1 ( ትግራይ ድንበሩ) ሶረቃ ወንዝ ነው ብለው ወሰኑ። እስካሁን ድረስ የእኛ ነው ብለውን በ2001 ዘመቻ አደረግን። የህወሓት ሚሊሻ በብአዴን ሚሊሻ ዝመት ተብሎ ተደናግረን አብረን ዘመትን። እንደገና በ2006 ዓም ዝመቱ ተባልን። ዘመትን። ያነም ሽቅብ ተኮሰ። እኛም ሽቅብ ተኮስን። ወንድማማቾች ነን አንገዳደልም ተባብለን ተለያየን። ፌደራል ይገባል ብሎ እያንጓለለን ይገኛል።
ከአማራ ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ ማንነት የሚጠይቁ አሸባሪ ናቸው ተብሎ ገበሬዎች በቅጥቀጣ ለይ ይኖራሉ። ……ድሮም የሚታወቀው ተከዜ ነው። በ83 ዓም ህወሓት ሲነግስ ለራሱ ነው የሰጠው እንጅ የወልቃይት ሕዝብ ወስኖ የሰጠው መሬት የለም።
ሰራተኛ ውል ገብቶ በአማርኛ ተፅፎ ወደ ክስ ሲገባ "ወደ ትግርኛ ቀይራችሁ አምጡት፣ አማርኛን ልናጠፋ እየጣርን ነው ብለው ሶስት መቶ፣ አራት መቶ ብር ከፍሎ ነው አማርኛን ወደ ትግርኛ የሚተረጎመው።
ከዚህ በኋላ ማንነቴን ሕገ መንግስት ይመልስልኛል። እሰዋለሁ፣ እጅ አልሰጥም፣ የተበተነ ንብረት ይበተን ብዬ ያን ጊዜ እንደወጣሁ በዳንሻ ዙሪያ በጫካው ሰንብቼ ወደዚህ ስደውል "ና" እንደናንተ ያሉ ሰዎች አሉ ማንነትክን ጠይቅ ሲሉኝ መጣሁ።
አሁንም ባድማችን አንለቅም። ባህላችንም አይደለም። መንግስትም እንዲያውቅልን። ሄደን ብንሞትም ከቤተ ክርስትያናችን፣ ከደብራችን መቀበር እንጅ በስደት አንቆምም። ……ማንነታችን ዛሬም አማራ ነው። ነገም አማራ ነው።
መጀመርያ ጊዜ ክልል 1 ( ትግራይ ድንበሩ) ሶረቃ ወንዝ ነው ብለው ወሰኑ። እስካሁን ድረስ የእኛ ነው ብለውን በ2001 ዘመቻ አደረግን። የህወሓት ሚሊሻ በብአዴን ሚሊሻ ዝመት ተብሎ ተደናግረን አብረን ዘመትን። እንደገና በ2006 ዓም ዝመቱ ተባልን። ዘመትን። ያነም ሽቅብ ተኮሰ። እኛም ሽቅብ ተኮስን። ወንድማማቾች ነን አንገዳደልም ተባብለን ተለያየን። ፌደራል ይገባል ብሎ እያንጓለለን ይገኛል።
ከአማራ ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ ማንነት የሚጠይቁ አሸባሪ ናቸው ተብሎ ገበሬዎች በቅጥቀጣ ለይ ይኖራሉ። ……ድሮም የሚታወቀው ተከዜ ነው። በ83 ዓም ህወሓት ሲነግስ ለራሱ ነው የሰጠው እንጅ የወልቃይት ሕዝብ ወስኖ የሰጠው መሬት የለም።
ሰራተኛ ውል ገብቶ በአማርኛ ተፅፎ ወደ ክስ ሲገባ "ወደ ትግርኛ ቀይራችሁ አምጡት፣ አማርኛን ልናጠፋ እየጣርን ነው ብለው ሶስት መቶ፣ አራት መቶ ብር ከፍሎ ነው አማርኛን ወደ ትግርኛ የሚተረጎመው።
የወልቃይት አማራ ተማሪዎች መከራ #5
አራተኛ ክፍል ነው። ክፍል ውስጥ አማርኛ ሲናገር ይገረፍ ነበር፣ ዛሬ ደግሞ ተፈናቃይ ሆኗል። ከወልቃይት ጠገዴ ከተፈናቀሉት የወልቃይት አማራ ተማሪዎች አንዱ ነው።
የወልቃይት አማራ መከራ #6
- አምስተኛ ክፍል ተማሪ ነው፣ በትርፍ ጊዜው ረዳትነት ይሰራል። በትምህርት ቤትም "ለምን አማርኛ ትናገራለህ?" እየተባለ ወከባ ይደርስበታል። በረዳትነቱን "ለምን በአማርኛ ትጠራለህ?" እየተባለ በማንነቱ ጥቃት ደርሶበታል። ተደብድቧል።
የወልቃይት አማራዎች ምሬት #7
- "ጠላታችን መሬታችን ነው። ለመሬት ብለው ነው የሚገድሉን"
- "አማራ እና አማርኛን ከምድረገፅ ለማጥፋት ነው"
- "ወልቃይት ጠገዴ ተወልዶ ያደገ መስርያ ቤት አይገኝም/አይቀጠርም። እንማራለን ይጥሉናል። አርሰን እንዳንበላ አድርገዋል።"
- "ለዚህ ያበቃን (የዶክተር አብይን) ቲሸርት ስለለበስን ነው፣ ‘የአብይ ልጅ ና’ ብለው የት እንደሚያደርሱት አይታወቅም።"
- "እስክስታ ስንመታ ከተገኘን አስረው አላስፈላጊ ቅጣት ይቀጡናል። ደረሰኝ የሌለው ቅጣት፣ከአንድ ወጣት 1000 ብር፣ 1500 ብር፣ በአንድ ወር 160 ሺህ ብር የወልቃይት ጠገዴ ወጣት ተቀጥቷል።"
- "አማርኛ አንድ ቃል፣ አንድ ልጅ አለ አማራ ነኝ ስላለ የተደበደበ፣ ከሞት ከትንሽ ነው የተረፈው። አማርኛ ስላወሩ ጥርሳቸው የረገፈ ጓደኞቻችን አሉ።"
- "አዲረመጥ ላይ፣ እኛ ሎጋው ሽቦ እያልን መዝለል ነው የምናውቀው፣ እነሱ እየዞራችሁ ጨፍሩ ይሉናል። በትግርኛ ዝፈኑ ነው የምንባል እኛ ግን አናውቀውም። አዲረመጥ እየዞራችሁ ጨፍሩ ሲባሉ እብይ ስላሉ አፍንጫው የተቆረጠ ልጅ አለ።"
- "ጠለሎ፣ አማርኛ ለሁለት አመት ተከልክሏል። 9ኛ እና 10 ኛ ክፍል። አማርኛ ቋንቋችን ነው። አማርኛ ግን ተከልክለናል። ለሁለት አመት ተከልክለው አልተማሩም።"
- "ፌደራል ገብቶ ልየ ኃይሉን ያስወጣል። (የዶክተር አብይ አህመድ ቲሸርት) ለምን ይቀደዳል። ዶክተር አብይኮ ለውጥ ያመጣ ሰው ነው። የታማኝ ለምን ይቀደዳል?"
0 Comments